Amesgigniwu አመስግኚው Mezmur / By Meaza Alemu Consolata Catholic Chuchu choir
0 Views
• 13/03/25
0
0
Embed
Bluegram
3 Subscribers
ዘማሪት መዓዛ አለሙ
ከኮንሶላታ ማሪያም ካቶሊካዊት ቤተ ጽሎት
Posted By Sam Carmel
አመስግኚው
አመስግኚው ነፍሴ ሆይ ተነሺ በዝማሬ
በዝማሬ እግዚአብሔርን ባርኪ
ነፍሴ ሆይ ስራውን ተርኪ
1. ከአፈር ከትቢያ ከውድቀት ያነሳሽ/2/ ነፍሴ ሆይ ተነሺ
የዛሬው አይደለም ያንቺ ማንነትሽ ስዕልሽ የጥንቱን አስቢ
ምስጋናን ዘምሪ ቅኔንም ደርድሪ/2/ ወጥተሸ አደባባይ
ንጉስ ለወደደው እንዲህ ተደረገ ተሰራ ብለሽ ለሰው አሳይ
2. እንደ ኃጥያትሽ ዋጋን አልከፈለሽ አልጣለሽ ጨክኖ አለሰበረሽ
ሀይሉን እንደሚያድስ እንደብርቱ ንስር አረገሽ በምህረቱ ምሮሽ
ፍቅሩ ገኖልሻል ለምስጋና ቁሚ ተነሺ መዝሙርን ዘምሪ
ቸርነት ማዳኑን ለሰው ልጆች አውሪ ንገሪ በይ ተነሽ አብስሪ
3. ውብ አርጎ አሳምሮ በፊቱ ያቆመሽ/2/ አይደለም በስራሽ
እንዲያው በፀጋው ነው እግዚ/ር የረዳሽ ያገዘሽ ይህን ቀን ያሳየሽ
በገና ደርድሪ ክራርን ከርክሪ/2/ ለባለውለታሽ
ምስክር ሁኚለት ምስጋናሽም ይመር አይነስ ላኮራሽ አምላክሽ
Show more
SORT BY-
Top Comments
-
Latest comments