//ረሱል ጃለሌ// አዲስ መድህ በሙአዝ ሀቢብ || New Menzuma Resul jalele @MuazHabibofficial

0 Views • 13/03/25
Share
Embed
Bluegram
Bluegram
3 Subscribers
3

ውድ የዩቱብ ቻናል ቤተሰቦቼ ትምህር ብቻ ሳይሆን ሙሀባንም ትወስዱበት ዘንድ ይህን የነብያችን ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለምን መድህ ጋብዣለሁ መልካም ግዜ


( ረሱል ጃለሌ ) ኑረል ሀዲ 2
ግጥም:- ዑስታዝ ሰዒድ
ዜማ:- ሙዓዝ ሀቢብ

።።።።።
አልሃምዱሊላህ፣ ሹክር ገለታ
ከላይ ከታቹ፣ ከየት እንዴታ
ለጠራው ጌታ
።።።።።

አጀብ እዝነቱ፣ ሞልቶ ሚፈሰው
ሙስጦፋን ሰጦ፣ ያን ትልቁን ሰው
ከውኑን አደሰው
።።።።።

ባንቱ ነው፣ የበራልን ሌቱ
ላንቱ ነው፣ ዜማየም ቅኝቱ
ያላንቱ፣ ማን አለኝ ሌላ (ሻፊዔ ጥላ ከለላ)
።።።።።።
።።።።።።።።።።።።

ያን ምቹ ስሙን፣ እስኪ ላድምቀው
መላ ነው ስሙ፣ መላ ለራቀው
ያዝ አትልቀቀው
።።።።

ያን የሚያምረውን፣ ጠባይም መልኩ
ያን የጠፋውን፣ አምሳያው ልኩ
ትንፋሹ ሚስኩ
።።።።።

ቢከትቡ፣ ቢንጠፈጠፍ ቀለም
ሲያዜሙም ቢኖሩ ዘላለም
ማን ችሎት ያንን ጀማላ (ቢለፋም ማዲሁ ሁላ)
።።።።።።
።።።።።።።።።።።።።

የከውኑን ሂላል፣ ያለም ረህመቱን
ያን የሰራውን፣ ልቤ ላይ ቤቱን
ጥኑ ናፍቆቱን
።።።።።

የመሀባው ጦር፣ ደርሶ ሚወጋው
ሚያወዛውዘው፣ ሰርክ ሚያፈጋው
የሸውቅ አደጋው
።።።

እጅግ ነው፣ አፍቅሮ ማይረጋው
ሲያለቅስ ሌቱን የሚያነጋው
ዛፍ ድንጋው ግዑዙ ሁላ
።።።።።
።።።።።።

ካልወዘወዘህ፣ ሲጠሩ አህመዱ
ካላስለቀሰህ፣ ሸውቁ መውደዱ
ታዘበህ ግንዱ
።።።።።

ወዳጅ ነን ብለን፣ የራቅነው ሁሉ
ምን ይለን ይሆን፣ ቢያየን ግመሉ
ዛፍ ድንጋ ሁሉ
።።።።።
መከተል፣ ነው እኮ መውደዱ
ታዲያ እንዴት፣ ይብለጠን ዛፍ ግንዱ
ለምንድን ቀረን ከኋላ
።።።።

አልሰማህም ወይ፣ ስሙ ሲነሳ
ህያው መግደሉን፣ ሟች እያስነሳ
ሰውም እንስሳ
።።።።

ቀላል ነው ባሉት፣ እየከረረ
ሰከነ በሚል፣ ነዶ እየናረ
መላው ቸገረ
።።።።

ማን አውቆ ይፍታው፣ ቢለፋም ቢጥር
ፍቅር ሚስጥሩ፣ ቀረ በሚስጥር
ማያዩት አጥር
።።።።።
ግመሉ፣ ወፍ አይቀር ሚዳቆ
አንበሳው፣ ተኩላ እንኳን አውቆ
ሚናፍቆ ያረሱለሏህ
።።።።።።

((ሃቢቡሏሂ))

መውደዱ ሃያል፣ ናፍቆቱ አይቻል
ስንቱ ዋለለ፣ ሲያቅተው መቻል
አፍቅሮ ማረፍ፣ ወዳጅ ያስተቻል
መተኛት ቀርቶ፣ መች ያንጎላቻል
።።።።።
አፊያ ነው ስንል፣ ጤናን ይነጥቃል
ህመም እንዳንል፣ ማዳንም ያውቃል
ቀርቧል ያሉ ለት፣ እጅግ ይርቃል
እዚ ሲያስለቅስ፣ እዚያ ያስቃል
መሀባ ማዕናው፣ መች ይታወቃል
።።።
ፍቅሩማ፣ ጠብታው ያጠልቃል
ይበርዳል፣ በል ሲለው ይሞቃል
ያላቃል ሩህን ከገላ
።።።።


።።።።።
።።።።።
ማዬት ቢሳነው፣ አይኑ ቢጠፋ
ሶሀባው መጣ፣ ወደ ሙስጦፋ
ቢያዝን ቢከፋ
።።።።።

ጨለመብኝ ቀን፣ ሃዘን ወረሰኝ
መሪ እንኳ የለኝ፣ መስጂድ ሚያደርሰኝ
አቅም አነሰኝ
።።።።።

አንቱ ኖት፣ የዝነቱ መፍለቂያ
መከራን ችግርን መራቂያ
መውደቂያ የለኝም ሌላ (ድረሱ አጣሁኝ መላ)
።።።።።
።።።።።።

አይዞህ አትዘን፣ አሉት ጀማላ
ውዱ አድርግና፣ ስገድ ለመውላ
አሁን ሂድና
።።።።

ከዚያም ለምነው፣ ጌታን ሶመዲ
አሽረኝ በለው፣ ከያዘኝ ጉዲ
በሙሐመዲ
።።።።።

ሚያሳምም ሚያድንም አሏህ ነው
ግን ስሜን ጠርቶ፣ ለለመነው
ወዲያው ነው ሃጃው ሚሞላ
(በኔማ እምቢ አይልም መውላ)
።።።።።።።
።።።።።።።

ሄዶ ቢፈፅም፣ ያሉትን ዘይኑ
በርቶለት መጣ፣ የጠፋው አይኑ
ጠፋ ሃዘኑ
።።።።።

ሁሉን አድራጊው፣ ማሊክ ሙሉካ
በነቢ ተብሎ፣ እምቢ አይልም ለካ
በሱ እንመካ
።።።።

ማን ታዬ እስኪ ባዶ ቀርቶ
ያፈረስ ማነው ነቢን ጠርቶ
መች ታይቶ ሃጃው ያልሞላ
።።።።።።።
።።።።።።።።።

( ሃቢቡሏሂ)

ሰይፉ ኻሊዱ፣ የማማ ሜዳ
አርማ ባንዲራ፣ ጨርቅ አሰናዳ
ብለው ፃፉበት፣ ያ ሙሐመዳ
ውጊያው ሲጫጫስ፣ ጦር ሲፈነዳ
ሁሉም ይል ጀመር፣ ያሙሐመዳ
ነቢን ሚከተል፣ መንገዱን አውቆ
በሄዱት ሚሄድ፣ ከራቁት ርቆ
ቢያሸንፍ እንጂ፣ መች ታዬ ወድቆ

/ ያንቱን ስም፣ ከፍ አርጎ አውለብልቦ
ኻሊድን፣ ሽንፈት እንዴት ቀርቦ
ድል በድል ሆኑ ሰይፉሏህ
።።።።

ናፍቆቴዋዬ፣ ዘመድ ወዳጂ
ላላፊ አግዳሚ፣ ምትከፍቱ ደጂ
የልቤ ብርሃን፣ ያይኔ ሲራጂ
ህመሜ አይሽርም፣ ባንቱ ስም እንጂ
።።።።።።


እንኳንስ የጅን፣ ካፍም የሰጡት
ያመኑት ሲክድ፣ ባኖሩት ሲያጡት
ሰው አልገኝ ሲል፣ እንዳስቀመጡት
ሰይዲ አንቱ ኖት፣ ማትለወጡት
ምትቀርፉት፣ ሃዘኑን ሁላ
።።።።

አያልቅ አያረጅ፣ አይዝል አይላላ
አዲስ ነው ዳኢም፣ ፊትም በኋላ
እንዳይረሳም፣ እንዳይሉት ችላ
ስር ሰዶ ዘልቋል፣ በደም በገላ
የውዱ መውደድ፣ መሀባውማ
ለምን አይባል፣ ከልካይ አይሰማ
ልብ ነው ቦታው፣ ቀዬ ከተማ
ሌላውን ሳላይ፣ ሌላን ሳልሰማ
ህይወቴ አድርጌ፣ ግብም አላማ
ልቤን ከሰጠሁ፣ ቆዬሁ እኔማ
።።።።።።



የኛው ሙሐመድ፣ የኔው ሙሐመድ
ፅልመት ይገፋል፣ መልኩ ሙሐመድ
ሃዘን ያጠፋል፣ ሳቁ ሙሐመድ
ዓይንን ይጠልፋል፣ ዓይኑ ሙሐመድ
ችግር ያረግፋል፣ ስሙ ሙሐመድ
ድል ያጎናፅፋል፣ ሱናው ሙሐመድ
።።።።

መሸም ሙሐመድ፣ ነጋም ሙሐመድ
ዛሬም ሙሐመድ፣ ነገም ሙሐመድ
አሁን ሙሐመድ፣ ኋላም ሙሐመድ
ሳርፍም ስቀመጥ ፣ስቆም ስራመድ
ስሙ ነው ወገን፣ ስሙ ነው ዘመድ

።።።

Show more
0 Comments sort Sort By